|
ፕሬዚዳንት ግርማ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንትን አነጋገሩ አዲስ አበባ, የካቲት 30 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ካርዲናል ኦስካር ሮድሪጌዝ ማራዲጋን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ ካርዲናል ኦስካር ሮድሪገዝ ማራዲጋዝ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው ካሪታስ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ እያከናወነ ባላቸው የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ነበር፡፡ bzþHM ድርጅታቸው ኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ያለችውን ልማት የማገዝ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በተለይም በትምህርት ዘርፍ ኢትዮጵያን ለማገዝ በሚያደርገው ጥረት በኢትዮጵያ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲን በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የማስፋፋት ፍላጎት አለው ማለታቸውን የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ብርሃነየሱስ በበኩላቸው ካሪታስ ኢንተርናሽናል በመላው ዓለም በ162 አገሮች የልማትና የበጎ አድርጎት ተግባራት ላይ እንደሚሳተፍ ገልጸዋል፡፡
|