“ፍቅርን በእውነት WS_” የtsኘውን የር.ሊ.ጳ መልዕክት በ¥ስመልkት  የአንድ ቀን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ተካሄd

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ሠራተኞች  ሚያዝያ 4 ቀን 2002 ዓ.ም “ፍቅርን በእውነት WS_ የተሰኘውን የብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛን ሐዋርያዊ መልዕክት አስመልክተው የአንድ ቀን ወርክሾፕ አካሂደዋል፡፡

በመልዕክቱ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት ክቡር አባ ዳንኤል አሰፋ የካፑቺን ፍራንሲስካውያን የፍልስፍናና ነገረመለኮት ተቋም ዳይሬክተር ናቸው፡፡

በወርክሾፑ ላይ ህገወጥ የሰው ልጆች ዝውውር፣ የሰው ልጅ ክብር፣ ፍትህና ሰላም በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ መላው የጽ/ቤቱ ሠራተኞችም ተካፋይ ሆነዋል፡፡

ወርክሾፑ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት የፍትህና ሰላም ክፍል የተዘጋጀ ነበር፡፡